ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– “ከአምባገነን መንግሥት ጋር አልሠራም” በማለት የዶክተር ዐቢይ አሕመድ መንግሥትን ከድተው የጁንታውን ቡድን የተቀላቀሉት፣ በህግ ተፈላጊና የጽንፈኛው ቡድን አባል የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግሥት እጅ ሰጡ።
ካለፈው አመት መጀመሪያ አንስቶ ፌደራል መንግሥቱን ከድተው በመቀሌ ከወንጀለኞች ጋር አብረው የመሸጉት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የህውሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግሥት ከፍተኛ ሓላፊነት የነበራቸው፣ እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት ያገለገሉ ናቸው።
ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የህወሓት ጁንታው ጥቅም ይሻለኛል ብለው ወደ መቀሌ ሲሸሹ፣ ሾፌራቸው ግን “የመንግሥትን ንብረት ለጁንታው አልሰጥም” በማለት መኪናውን ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ይዞ በመምጣት ማስረከቡ አይዘነጋም።
መንግሥት ሌሎች የህወሓት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እንደ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እጅ እንዲሰጡ ጥሪውን በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል።