እንግሊዝ ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሰኙ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቀደች

እንግሊዝ ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሰኙ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቀደች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– እንግሊዝ ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሰኙ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፍቃድ መስጠቷ ተሰማ።

ታላቋ ብሪታንያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ስትሰጥ ከምዕራባውያን ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ ስትሆን፤ ይህ ክትባት 95 በመቶ ፈዋሽነቱን የተረጋገጠ መሆኑን የብሪታንያ የበሽታ ተቆጣጣሪዎች መግለጻቸውን ተከትሎ በቀጣዩ ሳምንት ክትባቱ ለብሪታኒያውያን ይሰጣል ተብሏል።
የእንግሊዝ  መንግሥት 20 ሚሊዮን ሰዎችን መከተብ የሚችል 40 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት ማዘዙ የተሰማ ሲሆን ፤10 ሚሊየን ያህሉን በቀናት ውስጥ እንደሚረከብም ተነግሯል።

LEAVE A REPLY