ዶክተር ሂሩት ካሳው የ2019 የአፍሪካ ምርጥ ቱሪዝም መሪ ሆነው ተመረጡ

ዶክተር ሂሩት ካሳው የ2019 የአፍሪካ ምርጥ ቱሪዝም መሪ ሆነው ተመረጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የ2019  የአፍሪካ የቱሪዝም ምርጥ መሪ አሸናፊ ሆነው መመረጣቸውን በጋና የሚገኘው ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን የተሰኘው ድርጅት ገለፀ።

“እጅግ ምርጧ የአፍሪካ ቱሪዝም መሪ” ተብለው የተመረጡት ዶክተር ሂሩት በበኩላቸው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ  “በቱሪዝም፣ በሆቴልና መስተንግዶ በአጠቃላይ በዘርፋችን ላይ ለተሠማራችሁ እና ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራር በሙሉ እውቅናው የእናንተው ነውና እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉ ደስታቸውን አጋርተዋል።
የሽልማት ዝግጅቱ እ.ኤ.አ ታህሳስ 12 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY