ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመደመር ፖለቲካን ተንተርሶ የተቋቋመው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ይጀምራል፡፡
ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከነገ አርብ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በመደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
በተለይም በሰሞነኛው የትግራይ ክልል ሀይሎች ላይ የተወሰደውን ህግ የማስከበር እርምጃና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ይፋ አድርጓል።