አቢሲንያ ባንክ በአዲስ አበባ የመጀመሪያዎቹን ሰማይ ጠቀስ መንትያ ህንፃዎች ሊገነባ ነው

አቢሲንያ ባንክ በአዲስ አበባ የመጀመሪያዎቹን ሰማይ ጠቀስ መንትያ ህንፃዎች ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አቢሲንያ ባንክ ከሚድሮክ ተነጥቆ በምትክ በተሠጠው 10 ሺህ 329 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሰማይ ጠቀስ መንትያ ህንፃዎች ለመገንባት ዓለም ዐቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ተሰማ።

ባንኩ ከፍታቸው 50 እና 60 ወለል የሆኑ መንትያ ህንፃዎችን ለመገንባት በዲዛይን ቢውልድ (design build) ቀመር ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ዓለም ዐቀፍ ኮንትራክተሮች የጨረታ ግብዣ አቅርቧል።
አቢሲንያ ባንክ ያቀደው ግንባታ እውን መሆን ከቻለ መንትያ ህንፃዎቹ በከተማው ረጃጂሞቹ ህንፃዋች ከመሆናቸው ባሻገር፣ ዋና መሥሪያ ቤታቸውን ለመገንባት ዕቅድ ለያዙ የፋይናንስ ተቋማት መነሻ እንደሚሆን እየተነገረለት ነው።
ቦታው ቀደም ሲል ለዓመታት በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ስር በ ሁዳ ሪል ስቴት ተመዝግቦ የቆየ ሲሆን፤ በከተማው አምስት ከንቲባዎች እየተፈራረቁ ቦታውን ሲነጥቁ ሲመልሱ፣ ካርታ ሲያመክኑ እና ውል ሲያድሱ ቢቆዩም፣ ያለምንም ግንባታ ለ20 ዓመታት ቦታው ታጥሮ ለመሰንበት ተገዷል።

LEAVE A REPLY