ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአቶ አርከበ እቁባይ የቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ሙሉ በሙሉ ለግል ባለሀብቶች ሊሸጡ መሆኑ ተሰማ።
በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የወጣባቸውንና በተለያዮ ክልሎች የተገነቡት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር የተለያዩ ጥናቶች በመደረግ ላይ እንደሆኑ የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት አማካሪ ብሩክ ታዬ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ 13 ያህል ኢንደስትሪያል ፓርኮች የሚገኙ ሲሆን ከእነርሱ መካከል ዐሥሩ በሥራ ላይ ሲሆኑ፤ ኹለቱ በቅድመ ምስረታ፣ አንዱ ደግሞ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። በእነዚህ ኢንደስትሪያል ፓርኮች 60 ሺኅ የሚደርሱ ሠራተኞች ያሉ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ የኢንደስትሪ ፓርኮች በጨርቃጨርቅ ምርቶች ላይ የተሠማሩ ናቸው።