ቤተዛታ፣ አዲስ ሕይወትና ኮሪያ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ...

ቤተዛታ፣ አዲስ ሕይወትና ኮሪያ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አደረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ የኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ) በማድረግ የሚታወቁ ሦስት የግል ሆስፒታሎች የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ታማሚዎች በእጅጉ እየተጉላሉ ነው ተባለ።

የኩላሊት ዕጥበት (ዲያሊስስ) ሕክምና የሚሰጡ ሦስት የግል ሆስፒታሎች ለአንድ ጊዜ ዕጥበት ከ 150 እስከ 800 ብር ጭማሪ አድርገዋል ያሉት የኩላሊት ሕሙማን በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን አሰፋ፤ በዚህ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ በሚታይበት ወቅት የዋጋ ጭማሪው መደረጉ ታማሚዎችን የመኖር ተስፋቸውን ያመነምናል ብለዋል።
በዲያሊስስ አገልግሎት ላይ ቤተዛታ ሆስቲታል 150 ብር፣ አዲስ ሕይወት ሆስፒታል 500 ብር እና ኮሪያ ሆስፒታል 800 ብር ለአንድ ጊዜ ዕጥበት መጨመራቸውን ተከትሎ፤ አንድ የኩላሊት ታካሚ በሳምንት ሦስት ጊዜ ሕክምናውን ሲያደርግ ከ450 ብር እስከ ሁለት ሺኅ 400 ብር ተጨማሪ ወጪ በአንድ ሳምንት ውስጥ እንዲያወጣ መገደዱኔ ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY