ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ለ26 ለዓመታት በእምነታቸው ምክንያት ኤርትራ ውስጥ በእስር ላይ የቆዩ 28 የይሖዋ ምስክሮች እምነት ተከታዮች ከእስር ተፈቱ።
ኤርትራ ከ1987 ዓ.ም ገደማ ጀምሮ የይሖዋ ምስክሮች እምነት ተከታዮችን ዜግነት የሰረዘች ሲሆን ክስ ሳይመሰረትባቸው ለእስርም የተዳረጉት እነዚህ ሰዎች ከእስር የተፈቱት በውስጥ ትእዛዝ የተወሰነባቸውን የእስር ጊዜ በመጨረሳቸው እንደሆነ ተገልጿል።
የይሖዋ ምስክሮች ለእስር ከሚዳረጉባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ በአስገዳጁ የኤርትራ ወታደራዊ ብሔራዊ አገልግሎት የመሳተፍ ፍላጎት ስለሌላቸው ሲሆን፤ የእምነት ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አባላቱ ከአምስት እስከ 26 ዓመታት በእስር ካሳለፉ በኋላ መለቀቃቸውን ጠቁሞ፤ አሁንም 24 በእስር ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።