የሀዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የኢትዮ- ኬንያ የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ነገ ይመረቃሉ

የሀዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የኢትዮ- ኬንያ የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ነገ ይመረቃሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሀዋሳ ሞያሌ የ500 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ እና የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ነገ ተመራቂዎች ናቸው ተባለ።

የሀዋሳ ሞያሌ 500 ኪሎ ሜትር መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ሲፈጅ፣ የግንባታው ወጪ የተሸፈነው ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ ብድር መሆኑ ታውቋል።
በኬንያ በኩልም ከኢሲኦሎ እስከ ሞያሌ የሚወስደው የ503 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታም በመጠናቀቁ በነገው እለት የሚመረቅ ሲሆን፣ የመንገዶቹ ግንባታ የትራንስ አፍሪካ አውራ ጎዳ አንዱ አካል መሆናቸውም ተነግሯል።
የተገነቡት መንገዶች ከናይሮቢ ሞምባሳ እስከ አዲስ አበባ ያሉትን መንገዶች የሚያገናኘው የአፍሪካ አህጉር አቋራጭ የፍጥነት መንገድ አካል ናቸው።

LEAVE A REPLY