ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሲንቄ/ሲቆ ባህላዊ ሥነ ሥርዓት ምንነት እና በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ያላት ሚና በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መጽሐፍ ተመርቆ ለገበያ ቀረበ።
የግጭት መፍትኄ የህነችውን የሲንቄን ሥርዓት ለትውልድ ለማስተዋወቅ ብሎም ለትውልድ ለማስተላለፍ በጥናት ተደግፎ ለህትመት የበቃ መጽሐፍ መሆኑ በምረቃ ዝግጅቱ ላይ ተገልጿል።
የሀደ ስንቄ ባህላዊ ሥነ ሥርዓት ለሰላም የቆመ በመሆኑ ከአማርኛ ቋንቋ በዘለለ ባህላችንን ለዓለም ለማሳወቅ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እየተዘጋጀ ነው ያሉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው፤ የሰላም ምልክት የሆነችውን የሀደ ስንቄ በትር ከያዝን ጦርነቱ ወደ እርቅ ይቀየራል፤ ሰላም ምልክታችንም ይሆናል ብለዋል።