ብ/ ጀነራል አዳምነህ መንግሥቴን ጨምሮ አንድ ሺህ የሰሜን እዝ መኮንኖችን ጦሩ ጋር...

ብ/ ጀነራል አዳምነህ መንግሥቴን ጨምሮ አንድ ሺህ የሰሜን እዝ መኮንኖችን ጦሩ ጋር ተቀላቀሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የህወሓት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንግስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያህል የሰሜን እዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮነኖችን የአገር መከላከያ ሠራዊትና ፌደራል ፖሊስ በሠሩት አሰሳ ማስለቀቃቸው ታወቀ።

ጁንታው መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው አዴት በሚባል ቦታ አግቷቸው  መደበቁ ተደርሶበት በተደረገው አሰሳ ታጋቾቹ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበባቸው ለማስለቀቅ ተችሏል።
ሠራዊቱ ከጁንታው ካስለቀቃቸው መካከል የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንግሥቴ የሚገኙበት ሲሆን ሁሉም በአሁኑ ሰዐት ሰሜን እዝን መቀላቀላቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY