የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ያካሄደውን የመስክ ምልከታ ለፓርላማው ሪፖርት አቀረበ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ያካሄደውን የመስክ ምልከታ ለፓርላማው ሪፖርት አቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር የመስክ ምልከታ በተመለከተ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መግለጫ ሰጠ።

በመጀመሪያ ዙር የመስክ ምልከታው በባህርዳር እና በጎንደር በሲቪል አየር መንገዶች ላይ የሕወሓት ጁንታ ቡድን ያደረሰውን የሮኬት ጥቃት በቦታው በመገኘት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጉብኝት እንዳደረገ ገልጿል።
የማይካድራው ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ መሆኑን በመግለጽ በአንድ መቃብር በርካታ አስክሬን መቀበራቸውንም መርማሪ ቦርዱ በሪፖርቱ አስታውቋል።
የጽንፈኛው ቡድን ያስታጠቃቸው ኃይሎች በሱዳን ተጠልለው ባሉ ወገኞች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም ተነግሯል።

LEAVE A REPLY