ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የጁንታው ቡድን ከፍተኛ አመራር የነበሩት ዶክተር አዲስ ዓለም ባሌማ ፍርድ ቤት ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታወቀ።
በጥፋት ቡድኑ ውስጥ ተደራጅተው ጸረ ሰላም በሆነ እንቅስቃሴ ውስጥ ተገኝተዋል የተባሉት አምባሳደር አዲስ ዓለም ባሌማ፤ በመንግሥት ሹመኝነታቸው ወቅት ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማበላሸት እና ለማስቆም ተፅዕኖ ሲፈጥሩና ሢሠሩ እንደነበርም በክሱ ውስጥ ተገልጿል።
አዲስ ዓለም ባሌማ የመንግስት መረጃና ሚስጥሮችን አሳልፈው ሲሰጡ ነበር ያለው መርማሪ ፖሊስ፤ ከኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም መረጃ ሲለዋወጡ እና የመንግስትን ምስጢር አሳልፈው በመስጠት ለተፈፀሙ ወንጀሎች በጋራ ሰወጥኑና ሲተግብሩ ነበር ብሏል።