ለድንበር አሽከርካሪዎችና ረዳቶቻቸው ከኮሮና ጋር በተያያዘ የሕይወት መድን ሊገባላቸው ነው

ለድንበር አሽከርካሪዎችና ረዳቶቻቸው ከኮሮና ጋር በተያያዘ የሕይወት መድን ሊገባላቸው ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከኮቪድ-19 ቫይረስ ጋር በተያያዘ ለድንበር ተሻጋሪ አሽከርከሪውችና ረዳቶቻቸው የሕይወት መድን ሊገባላቸው መሆኑ ተሰማ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንደገለጸው ከሆነ ከዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ከተካሄደ በኋላ መሆኑንም አስታውቋል።
በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እውን ይሆናል የተባለው የሕይወት መድን በባለንብረቶች እና በመድን ኩባንያዎች በሚከፈል የአረቦን መጠን የሚሸፈን ነው ተብሏል።
የመድን ዋስትናው አሽከርካሪዎቹ እና ረዳቶቻቸው በኮሮና ቫይረስ የተነሣ ሕይወታቸው ሲያልፍ ለአሽከርካሪዎቹ ቤተሰብ 250 ሺህ፣ ለረዳቶቹ ቤተሰብ ደግሞ 150 ሺህ ብር ካሣ ያስገኛል።

LEAVE A REPLY