ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ በምርጫ መታዘብ ሥራ መሳተፍ ለሚፈልጉ ሲቪል ድርጅቶች ጥሪ...

ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ በምርጫ መታዘብ ሥራ መሳተፍ ለሚፈልጉ ሲቪል ድርጅቶች ጥሪ አቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥድሥተኛው ሀገራዊ በምርጫ መታዘብ ሥራ መሳተፍ ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥ ሲቪል ማህበረሰብ  ድርጅቶች ጥሪ አቀረበ።

በቀጣዮ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ  ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች መሳተፍ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ገለልተኛ ምርጫ እንዲኖር በማድረግ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አምናለሁ ያለው ቦርዱ በዚህ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁሟል።
ለትርፍ ያልተቋቋሙ፣ የመንግስት አካል ያልሆኑ እና በህግ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወገንተኝነት ነጻ የሆኑ፣ እንዲሁም የተቋማቸው የቦርድ አባላት እና መሪዎች የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑ  ይችላሉ ያለው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የምርጫ መታዘብን ሥራ ለመወጣት የሚያስችል ብቃት ያላቸው እና የሚያሰማሯቸው ታዛቢዎችም ምርጫን በገለልተኝነት ለመታዘብ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸውም አሳስቧል።

LEAVE A REPLY