ማይጨው ላይ በተካሄደ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ከባድና ቀላል መሳሪያዎች ተያዙ

ማይጨው ላይ በተካሄደ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ከባድና ቀላል መሳሪያዎች ተያዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍትሻ ከ426 ሺኅ በላይ የክላሽ ጥይት፣ ከ3 ሺኅ 500 በላይ የብሬን ጥይት፣  በርካታ ቁጥር ያላቸው ክላሽንኮቭና ሽጉጦች፣ ከ1 ሺኅ 100 በላይ ልዩ ልዩ የእጅ ቦንቦች ተያዘ።

በሰሜን ዕዝ የ32ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል መላኩ ገላነህ ፤ በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውንና ከተማዎችን የጦርነት አውድማ ለማድርግ፣ ዜጎችን ለከፋ ችግር ለማጋለጥ በማለም ሠራዊት በህግ የሚከለከልባቸው ቦታዎች ተለይተው እንደነበርም አስረድተዋል።
በእምነት ተቋማት፣ በመማሪያ ክፍሎች፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማትና በመንግሥት መስሪያ ቤቶች በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ተከማችቶ በፍተሻው መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY