ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ክልል ሰብኣዊ እርዳታ ለማቀረብ የሚደረገው ጥረት በውጊያ ምክንያት እንደተስተጓጎለ ተደርጎ የሚነገረው እውነት እንዳልሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
በአሁኑ ወቅት እየሸሹ ያሉ የወንጀለኛው ቡድን አባላትን አድኖ ለመያዝ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አልፎ አልፎ ከታጣቂዎች ጋር የሚደረግን የተኩስ ልውውጥን እንደ ውጊያ አድርጎ ማቅረብ ተገቢ እንዳልሆነም ተገልጿል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ይህን ይበል እንጂ የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ መንግሥታ ጋር ስምምነት ቢፈጽምም በክልሉ የተለያዮ ቦታዎች በሚካሄድ ውጊያ ምክንያት እርዳታ ለማቅረብ የማደርገው ጥረት ተስተጓጉሎብኛል ሲል መግለጹ አይዘነጋም።