ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም ትኩረት ሰጥቻለሁ አለች

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም ትኩረት ሰጥቻለሁ አለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው ተባለ።

በአየር ንብረት ላይ ባተኮረው የቪዲዮ ኮንፍረንስ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሠራች እንደሆነ አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ትኩረት ሰጥታ እየሠራች እንደሆነ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እስከ ፈረንጆቹ 2030 ከካርቦን ልቀት ነጻ የሆነ ኢኮኖሚን ለመገንባት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በ10 ዓመት የልማት እቅድም አስተማማኝ ኢኮኖሚ ለመገንባት ማቀዷንና
የፓሪስ ስምምነትን በማክበር ኢትዮጵያ  የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ የ15 ዓመት እቅድ መንደፏንም ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY