ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ ወዲህ በክልሉ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ሁኔታ በእጅጉ ያሳሰበው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት ውስጥ በስደት ትግራይ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ግድያ ከመፈጸም ባሻገር እየታፈኑ ወደ ኤርትራ እየተወሰዱ መሆናቸውን ተከትሎ በርካታ ኤርትራውያን ወደ አዲስ አበባ በመሸሽ ላይ መሆናቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።
በኤርትራውያኑ ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እየተጣራ መሆኑን ያመላከተው መግለጫ፤ በትክክልም የተባሉት ነገሮች ተፈጽመው ከሆነ ከፍተኛ የዓለም ዐቀፍ ህግ ጥሰት እንደሆነ በዝርዝር ለማሳወቅ እገደዳለሁ ብሏል።
መግለጫውን አስመልክቶ ምላሽ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት መረጃው የተሳሳተ መሆኑን ቢያስተባብልም የተወሰኑ ኤርትራውያን ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ ግን አምኗል።