ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ አብደላ ሃምዶክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።
ኢትዮጵያና ሱዳን የሁለትዮሽ እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ከማጠናከር በተጨማሪ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር በጋራ እየመከሩ መሆናቸውም ተነግሯል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ደጋግሞ መምጣትና ዶክተር ዐቢይ አሕመድም ወደ ስፍራው ደጋግመው መጓዛቸው የኢፊዲሪ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል በሚገኘው ጽንፈኛ ቡድን ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ጋር አስቀድሞ የታለመ ነገር መኖሩን ያመላክታል እየተባለ ነው።
በአሁን ሰዐት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተለያዮ ስፍራዎች ገብተዋል የተባሉ የጁንታው የጥፋት ኃይሎችን በተመለከተ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ምስጢራዊ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ተገምቷል።