ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የተለያዮ ሀገራት በመሄድ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥራ እየሠሩ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዳዝንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሥራ ጉብኝት ኮቲዲቯር አቢጃን መግባታቸው ተሰማ።
ሳህለወርቅ ወደ ኮትዲቯር ያመሩት በኮትዲቯሩ ፕሬዝዳንት አላሳኔ ኦታራ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ይሁን እንጂ በቆይታቸው በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያም ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በኮትዲቯር ቆይታቸው ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉና በምዕራብ አፍሪካ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት እንደሚኖራቸው የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል።