ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በህወሓት አባላት፣ ቤተሰቦቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከልማት ባንክ ባለፉት አመታት በብድር መልክ ወስደው መሰወራቸው ተነገረ።
የማፍያ ቡድን ሆኖ በዚህች ሀገር ለ27 አመታት የዘለቀው በነበረው ከፍተኛ የቤተሰባዊ ትስስር አሠራር በተለያዮ የሀገሪቱ ክፍሎች ራሱን ጨምሮ በቅርብ ሰዎቹና በቀንደኛ ደጋፊዎቹ አማካይነት ከፍተኛ የሆነ የሀብት ምዝበራ ለኪሳራ በተጋለጠው ልማት ባንክ ላይ መፈጸማቸው ይፋ ተደርጓል።
የጁንታው አባላት ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በመፈጸም በጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ፣ በሁመራና በተለያዮ አካባቢዎች በተቆጣጠራቸው ሠፋፊ የእርሻ መሬቶችን ማስያዣ በማድረግ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠር ብድር በመውሰድ የውሃ ሽታ መሆናቸው በተካሄደው ጥናት ተረጋግጧል።
እነዚህ በማኒፋክቸሪንግና በእርሻ የተሠማሩ ባለሀብቶችን ጉዳይ በተመለከተ ባንኩ ለብድር ማካካሻ የባለሀብቶችን ንብረት ቢረከብም መልሶ ገንዘቡን የማግኘቱ ነገር ግን እንደሰማይ የራቀው መሆኑ ታውቋል።