ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙና የልደት ካርድ ለሌላቸው ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የልደት ካርድ ሊሰጥ ነው ተባለ።
ብዙ ነዋሪዎች ከትኩረት አለመስጠትና ከሰነድ አያያዝ ጋር በተገናኘ የልደት ሰርተፍኬት ሳይዙ እስካሁን ለመቆየት መገደዳቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አሁን ላይ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የልደት ካርድ አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር ግርማ መኮንን ፤ የልደት ካርድ ማለት የአንድን ግለሰብ ትክክለኛ ዕድሜ ከማወቅም በዘለለ ለአንድ ሀገር የተስተካከለ የሕዝብ ብዛት ለማወቅ ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሠሩ ፣ ልጁ መብቱ እንዲከበርለት የሚያስችለው ፣ ዜግነት የሚያገኙበት አሠራር እንደሆነ ገልጸዋል።