ኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እስር ከጨመረባቸው ሀገራት 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

ኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እስር ከጨመረባቸው ሀገራት 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– እየተገባደደ ባለው የፈረንጆች ዓመት 2020 በተለያዩ የዓለም ሀገራት 270 ጋዜጠኞች መታሰራቸውን  ዓለም ዐቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ሲፒጄ አስታወቀ።

በርካታ ጋዜጠኞች የታሰሩት ሥለ ኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት፣ ሥለ ሕዝባዊ ተቃውሞና ፖለቲካዊ ቀውስ በመዘገባቸዉ ነዉ ያለው ሲፒጄ፤  የታሠሩ ጋዜጠኞችን ብዛት፣ የታሰሩባቸውን ምክንያቶችና ሥፍራዎች እስካጠናቀረበት እስካለፈዉ ሕዳር ድረስ 274 መድረሱንም ይፋ አድርጓል።
በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ቻይና፣ ግብፅና ሳዑዲ አረቢያ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለዉን ደረጃ ይዘዋል። ከሦስት ዓመታት በፊት ገደማ አካባቢ በርካታ ጋዜጠኞችን በመፍታት የተደነቀችዉ ኢትዮጵያ ዘንድሮ የታሳሪ ጋዜጠኞች ቁጥር ከጨመረባቸዉ ሁለት ሀገራት አንዷ ሆናለች።

LEAVE A REPLY