ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በተሳሳተ መረጃ በትግራይ ክልል ካሉ የስደተኞች ካምፕ የወጡ ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ ካምፕ በመመለስ ላይ ናቸው ተባለ።
በትግራይ ክልል በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የተሳሳተ መረጃ ደርሷቸው ወጥተው የነበሩ ስደተኞች ወደ መጠለያቸው ተመልሰዋል ያለው በኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ነው።
ስደተኞች በሚገኙባቸው አካባቢዎች መከላከያ ሠራዊት ተገቢውን ሰላም የማስከበር ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከስደተኞች ጋር በተደረሰ ስምምነት 581 ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ ማይ ዓይኒ እና አዲ ሓሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች በሰላም እንዲመለሱ ተደርጓል።