የድምፅ ብክለት ያደረሱ 11 መጠጥ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች በአዲስ አበባ ታሸጉ

የድምፅ ብክለት ያደረሱ 11 መጠጥ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች በአዲስ አበባ ታሸጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ከ100 በላይ መጠጥ ቤቶች ላይ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ባለሙያዎች ባደረጉት የድምፅ ልኬት መሠረት እርምጃ ተወሰደ።

አካባቢውን መበከላቸው የተረጋገጠው መጠጥ ቤቶች የማስተካከል እርምጃ እንዲወስዱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዉ አብዛኛዎቹ መጠት ቤቶች ቢያስተካክሉም ፣ 11 የሚሆኑት መጠጥ ቤቶች የሚለቁትን የድምጽ መጠን ባለማስተካከላቸዉ እንደታሸጉ ተደርጓል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በአቂቃ ቃሊቲ ክፍል ከተማ የሚገኙት 11 መጠጥ ቤቶች ከተፈቀደዉ 45 ዴስባል የድምፅ መጠን በላይ አልፍዉ እሰከ 85 ዴሲባል መጠን ሲጠቀሙ ተገኝተዋል ነው የተባለው።
በቀጣይም በአካባቢ ላይ ብክለት የሚያደረሱ ኢንዱስትሪዎች ፋብሪካዎች፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መጠጥ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ ህጉ በሚፈቅደዉ መሠረት እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

LEAVE A REPLY