በአ/አ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በጠቅላላ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

በአ/አ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በጠቅላላ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከእነዚህ ተሽከርካሪዎች ውስጥ ሕጋዊ እውቅና የሌለው የራሳቸውን ታርጋ ለጥፈው የሚንቀሳቀሱ መኖራቸውም ተረጋግጧል ነው የተባለው።

ማንኛውንም ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ በሰዐት ከ40 እና ከዛ በላይ የሚጓዙ፣ ያለ ሰሌዳ ቁጥር መንቀሳቀስ እንደማይችሉ በ2011 የወጣ መመሪያ መውጣቱን ተከትል አሁን ተሽከርካሪዎቹን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ይፋ አድርጓል።
በሞተር ብቻ የሚሠሩ፣ በኤሌትሪክ ኃይል የሚሠሩ፣ በጸሐይ ኃይል የሚሠሩ እንዲሁም በፔዳል የሚሠሩትን ጨምሮ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በጠቅላላ በቁጥጥር ላይ እያዋሉ እንደሆነና ይህም አግባብነት ያለው የሕግ ማስከበር ሥራ መሆኑን የትራንስፖርት ቢሮ ሓላፊ ስጦታው አካለ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY