ጳውሎስ ሆስፒታል በዘር ለሚተላለፍ በሽታ አዲስ ሕክምና እጀምራለሁ አለ

ጳውሎስ ሆስፒታል በዘር ለሚተላለፍ በሽታ አዲስ ሕክምና እጀምራለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጳውሎስ ሆስፒታል በዘር ለሚተላለፍ በሽታ አዲስ ሕክምና ሊጀምር መሆኑ ተሰማ።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተፈጥሮ ከእናት እና ከአባት በዘር የሚተላለፍ Cystic fibrosis የተባለ የመተንፈሻ አካላትን የሚጎዳ በሽታን ለመመርመር ሥራ እንደሚጀምር መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አስታውቋል።
እስካሁን ድረስ ሕክምናውን ለመመርመር የሚያስችል ምንም ዓይነት የመመርመሪያ መሳሪያ ሀገር ውስጥ ያልነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን መሳሪያውን ከመካከለኛው ምስራቅ Cystic fibrosis ማኅበር በእርዳታ መልክ በመገኘቱ በአሁኑ ወቅት መሳሪያው በሆስፒታሉ ተገጥሞ ሥራ ይጀምራል ተብሏል።

LEAVE A REPLY