በትግራይ ክልል ነዋሪዎች የጦር መሳሪያ እንዲያስረክቡ የተቀመጠው ጊዜ ገደብ ተጠናቀቀ

በትግራይ ክልል ነዋሪዎች የጦር መሳሪያ እንዲያስረክቡ የተቀመጠው ጊዜ ገደብ ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የትግራይ ክልል ነዋሪ የጦር መሳሪያዎችን እንዲያስረክብ አዲሱ አስተዳደር  ያሰቀመጠው የጊዜ ገደብ ተጠናቀቀ።

በሕጋዊም ሆነ በሕገ ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ነዋሪዎች እስከ ትናንት ማክሰኞ ታኅሳስ 6/2013 ዓ.ም ድረስ መሳሪያቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የጸጥታ አካላት እንዲያስረክቡ ትእዛዝ ቢወጣም አሁንም በርካታ ነዋሪዎች መሳሪያዎችን እንዳላስረከቡ ታውቋል።
ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እንደሚሰበሰቡ ያስታወቀው ጊዜያዊ አስተዳደር፤ በፍተሻው ትጥቅ የሚገኝባቸው ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ገልጿል።

LEAVE A REPLY