ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ዓመት ብቻ ወደ ውጪ ከላከችው የፕላስቲክ ተረፈ ምርት 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማግኘቷ ተሰማ።
ዓለም ዐቀፉ የምግብና መጠጥ አምራች ኔስሌ ደግሞ ከአካባቢ ዘላቂነት አማካሪው ቲ.ኤስ. ኢንቫዮርመንት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ቆሻሻ ማስወገጃ መርኃ ግብር ማዘጋጀቱና የመርኃግብሩ ዓላማ በሚቀጥሉት 12 ወራት የፕላስቲክ ገለልተኛነትን ማሳካት እንደሆነ ታውቋል።
ኔስሌ በተሸጡት ምርቶቹ ያለውን ፕላስቲክ በመሰብሰብ ተጨማሪ የፕላስቲክ ፍሰት ወደ ቆሻሻ መጣያ እንዳይገባ ያደርጋል ያለው መረጃ፤ ኔስሌ በዓለም ትልቁ የምግብ እና የመጠጥ አምራች ኩባንያ እንደመሆኑ መጠን፣ የፕላስቲክ ቆሻሻን ችግር በመቋቋም ረገድ የመሪነት ሚናውን ለመወጣት ቁርጠኛ እንደሆነም አስረድቷል።