ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ ለሚያደርገው የበጀት ድጋፍ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዮሮ ወይም 110 ሚሊዮን ዶላር የሚሰጠው ያስቀመጣቸው ሁኔታዎች ተግባራዊ ሲሆኑ ብቻ እንደሚሰጥ አስታወቀ።

አሁን ባለው ሁኔታ የአውሮፓ ሕብረት የበጀት ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው የአውሮፓ ሕብረት፤ የበጀት ድጋፉ የሚለቀቀው ቀድሞ ስምምነት የተደረሱባቸው ጉዳዮች መሟላታቸው ሲረጋገጥ እና እንደአስፈላጊነቱ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ከገቡ በኋላ መሆኑን አስታውቋል።
በዓለም  ዐቀፍ ሕግ መሠረት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሰዎች ድጋፍ እንዲያገኙ የሰብዓዊ እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች እንዲገቡ ፍቃድ ሲሰጥ፣ተከስተዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር የሚያስችል የአሠራር ዘዴ ሲዘረጋ፣መገናኛ ብዙኃን ወደ ትግራይ እንዲሄዱ ሲፈቀድ እና በትግራይ የግንኙነት መስመሮች ሙሉ በሙሉ ሲከፈቱ ገንዘቡ ይለቀቃል ተብሏል።

LEAVE A REPLY