አውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ኬንያ 23 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ አደረገ

አውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ኬንያ 23 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት ሀገራት የ23 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን አድርጊያለሁ አለ።

በሕብረቱ መግለጫ መሠረት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያና ሱዳን የእርዳታው ተቋዳሽ ሆነዋል።
ከ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ውስጥ 18 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮው በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል ሲሆን፣ ሁለት ሚሊየን ዩሮው ደግሞ ለሱዳን የተደረገ ድጋፍ ነው ተብሏል።
ቀሪው 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዮሮ የሚሆነው ገንዘብ በኬንያ የምግብ ዋስትና ለተጋረጠው አደጋ የሚውል ነው። የአውሮፓ ሕብረት በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ 63 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ መድረሱን አስታውቋል።

LEAVE A REPLY