ትግራይ አሁን 95 በመቶ ሕግና ሥርዓት እየተተገበረባት እንደሆነ አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ገለጹ

ትግራይ አሁን 95 በመቶ ሕግና ሥርዓት እየተተገበረባት እንደሆነ አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና አሁን ላይ ያለችው ትግራይ የአምባገነኑ ጁንታ እንቅስቃሴ እምብዛም የማይታይባት 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት መሆኗን አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ገለጹ።

የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ፤ የህወሓት ጁንታ ከአሁን በኋላ እንደማይመለስና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ገሀነም መውረዱን በመገንዘብም ደጋፊዎችና አባሎቻቸው ወደ ህዝባቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲመሰርቱ መልእክት አስተላልፈዋል።
” አሁን ትግራይ በአጠቃላይ 95 በመቶ ህግና ሥርዓት የተተገበረባት ሆናለች። የአምባገነኑ ጁንታ እንቅስቃሴ የሚታይበት ሁኔታ ብዙም የለም። አውሮፕላንን ጨምሮ ትራንስፖርት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይንቀሳቀሳል” ሲሉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የገለጹት አቶ ሊላይ፤ በሚቀጥለው ሳምንትም የባንክ አገልግሎት በሰፊው ይጀመራል ብለዋል።

LEAVE A REPLY