ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አዲስ የተራባው የበረሃ አንበጣ መንጋ ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሶማሌ አካባቢ ባደረገው የመስክ ምልከታ መረረት ወቅታዊ የአየር ሁኔታ ለመራባት ምቹ በመሆኑ በምስራቅ ኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ሰፊ እርባታ እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።
በግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ በላይ ንጉሴ በመራባት ላይ የሚገኘው ይህ የበረሃ አምበጣ መንጋ ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ መሆኑን ከስፍራው ሆነው ይፋ አድርገዋል።
በሶማሌ ክልል፣ በምስራቅ ኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በ13 አውሮፕላኖች የኬሚካል ርጭት ከወዲሁ መጀመሩን የጠቆሙት ሓላፊው፣ በመኸር ሰብል ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት እንደማይኖርም አስረድተዋል።