በያዝነው ዓመት 100 ለኩላሊት እጥበት የሚያገለግሉ ማሽኖች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተባለ

በያዝነው ዓመት 100 ለኩላሊት እጥበት የሚያገለግሉ ማሽኖች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና  ባለንበት 2013 ዓ.ም ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢዎች ጋር በመሆን 100 ለኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ ) ሕክምና የሚያገለግሉ ማሽኖች ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ ተባለ።

የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢዎች ኤጀንሲ ጋር በመሆን ለጉዳዮ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ተከትሎ ነው የማጠቢያ ማሽኖቹ እንደሚገቡ ተነግሯል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ የዲያሊስስ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው የኩላሊት ታማሚዎች መብዛትን ተከትሎ በያዝነው አመት በተያዘው እቅድ መሠረት 100 ያህል የኩላሊት ዕጥበት ሕክምና ለመስጠት የሚያስፈልጉ ማሽኖችን ለማስገባት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY