በመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮችን በቁጥጥር ሥር...

በመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮችን በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ሥር ማዋል መጀመሩ ተገልጿል።

ከችግሩ ጋር በቀጥታ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ የቀድሞ ባለስልጣናት በስም የተጠቀሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ፡ –

1ኛ. አቶ ቶማስ ኩዊ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ

2ኛ. አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር

3ኛ. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡-የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር

4ኛ. አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

5ኛ. አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ

እነዚህ አመራሮች ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር እጃቸው እንዳለበት በመረጋገጡ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ወደ ሠላም ለመመለስ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲደግፍ የክልሉ መንግስት ጥሪ ማቅረቡን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

LEAVE A REPLY