ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ሱዳን በኮሮና ቫይረስ ልውጥ ዝርያ ስጋት መነሻ ከብሪታንያ ከኔዘርላንድስ እና ከደቡብ አፍሪካ ተጓዦች እንዳይመጡባት ከለከለች።
ክልላው እስከ ታህሳስ 27 እንደሚዘልቅ ሬዲዮ ዳባንጋ በድረ ገፁ ያሰፈረ ሲሆን፤ በኔዘርላንድስም በብሪታንያ በስፋት በመሰራጨት ላይ በሚገኘው ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተሰምቷል።
ይህን ተከትሎም የሱዳን ሲቪል አቪየሽን ከብሪታንያ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ኔዘርላንድስ መንገደኞች እንዳይመጡ የተላለፈውን ውሳኔ እንዲያስፈፅም ጥብቅ መመሪያ እንደተሰጠው ለማወቅ ተችሏል።