በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ “ትንሿ ኢትዮጵያ” ለሚባለው አካባቢ የተሰጠው ስያሜ ህጋዊ እውቅና አገኘ

በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ “ትንሿ ኢትዮጵያ” ለሚባለው አካባቢ የተሰጠው ስያሜ ህጋዊ እውቅና አገኘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ሊትል ኢትዮጵያ (ትንሿ ኢትዮጵያ) ለሚባለው አካባቢ የተሰጠው ስያሜ ህጋዊ አውቅና አገኘ።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋ፤ የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አስተዳደር እና የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለ”ትንሿ ኢትዮጵያ” እውቅና እንዲያገኝ ላበረከቱት ድጋፍና አስተዋፅኦ በመንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል።
እውቅናው ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማሳደጉም በላይ፣ በማኅበራዊ እና በባህላዊ ጉዳዮች ወዳጅነታቸውን እንደሚያጎለብተው አምባሳደሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY