በቤኒሻንጉል ከ27 ሺኅ በላይ ዜጎች ምንም አይነት የምግብ እርዳታ አልተደረገልንም አሉ

በቤኒሻንጉል ከ27 ሺኅ በላይ ዜጎች ምንም አይነት የምግብ እርዳታ አልተደረገልንም አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በቤኒሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ ታኅሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት ተፈናቅለው ቡለን ከተማ የሚገኙ በርካታ ዜጎች እርዳታ አላገኙም ተባለ።
መንግሥት በስፍራው ላሉ ዜጎች እርዳታ እያደረግሁ ነው ቢልም እየወጡ ያሉ መረጃዎች ግን ከ27 ሺሕ በላይ ዜጎች አስፈላጊው እርዳታ እየተደረገላቸው ባለመሆኑ በምግብ ዕጦት መቸገራቸውን ያሳያሉ።
በታጣቂዎች በንጹሓን ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት አካባቢያቸውን ለቀው ከ20 እስከ 30 ኪሎ ሜትር ተጉዘው ቡለን ከተማ የሚገኙ ከ27 ሺሕ በላይ የኩጅ ቀበሌ ተፈናቃዮች ወደ ከተማዋ መግባት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ፤ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከየቤቱ ምግብ አሰባስቦ እየመገባቸው እንደሆነ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY