የሮይተርስ ካሜራ ማን ኩመራ ገመቹ አዲስ አበባ ውስጥ መታሰሩ ተሰማ

የሮይተርስ ካሜራ ማን ኩመራ ገመቹ አዲስ አበባ ውስጥ መታሰሩ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የዓለም ዐቀፉ የዜና አውታር የሮይተርስ የካሜራ ባለሙያ የሆነው ኩመራ ገመቹ፣ አዲስ አበባ ከሚገኘው የመኖሪያ ቤቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ።

የካሜራ ባለሙያው ባለፈው ሐሙስ፣ ታኅሣስ 15/2013 ዓ.ም መሆኑን የገለጸችው ባለቤቱ ሀዊ ደሳለኝ፤ በምን ምክንያት በፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ ምታውቀው ነገር አለመኖሩንም ጠቁማለች።
 ሮይተርስም የእስሩን ምክንያት ለማወቅ ለፖሊስ ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ጠቁሞ እስካሁን ድረስ ኩመራ ላይ ክስ አለመመስረቱንም ይፋ አድርጓል።
ሮይተርስ ይህን ይበል እንጂ ኩመራ አርብ ታህሳስ 16/2013 ዓ.ም ያለ ጠበቃ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀን በመጠየቁ ችሎቱ እንደፈቀደለት ገልጻለች።

LEAVE A REPLY