በመርፌ መልክ የተዘጋጀው የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት ለኬንያ ሴቶች ሊሰጥ ነው

በመርፌ መልክ የተዘጋጀው የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት ለኬንያ ሴቶች ሊሰጥ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በመርፌ መልክ የተዘጋጀው የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት ለኬንያ ሴቶች ሊሰጥ መሆኑ ተሰማ።
መድኃኒቱ በየ2 ወሩ አንድ ጊዜ የሚወሰድ ነው ያለው ዘ ስታር፤ ቀደም ሲል በመድኃኒቱ ላይ በተደረገው ሙከራ ከ3000 በላይ ሴቶች እንደተካፈሉና አሁን ለመድኃኒቱ ተጠቃሚነት ቅድሚያ የተሰጣቸው በሙከራው የተካፈሉት እነዚህ ሴቶች መሆናቸውን ገልጿል።
ካቦቴ ግራቪር የተሰኘው በመርፌ በየ2 ወሩ በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት ጥቅም ላይ ሲውል በየዕለቱ የሚወሰደውን የፀረ HIV እንክብል ያስቀረዋል እየተባለ ነው።
ከኬንያ በተጨማሪ ደቡብ አፍሪካ፣ ማላዊ፣ ቦትስዋና፣ ዚምባብዌ እና ኢስዋቲኒ በመርፌ በየ2 ወሩ የሚሰጠው የፀረ  HIV መድኃኒት የተሞከረባቸው ሀገራት ሆነዋል።

LEAVE A REPLY