ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሁለት ተጨማሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረዛቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦሕዴፓ) እና የሲዳማ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሲብዴፓ) ተሰራዦቹ ፓርቲዎች ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታህሳስ ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ መሠረት ማሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተጠየቁት መካከል 4 ፓርቲዎች መስፈርቱን ያሟሉ ሲሆን 2 ፓርቲዎች ደግሞ ባለሟሟላታቸው ለመሰረዝ መገደዱን ገልጿል።
የቀረበውን መስፈርት በማሟላት ያጠናቀቁት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)- 39%፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ (አሕፓ) 45%፣ የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ) – 94%፣ የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ (አነግፓ) 48%
መሆናቸውን ቦርዱ ይፋ አድርጓል።