ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የ4 የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ።
በዚህ መሠረት በምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳባቸው
1. አቶ አድጎ አምሳያ
2. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ
3. አቶ ግርማ መኒ
4. አቶ አረጋ ባልቢድ መሆናቸው ታውቋል።
ግለሰቦቹ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተደረገው ሰሞኑን በመተከል ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተከትሎ መሆኑ ታውቋል።
በተያያዘም አቶ ሙሳ ሃሚድ፣አቶ አትንኩት ሽቱን ጨምሮ የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ ከጥቃቱ ጋር ተጠርጥረው የታሰሩ ሲሆን ሌሎች ስድስት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተመልክቷል።