ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ በመቀሌ የሚገኘውን የፓርቲውን ዋና ጽሕፈት ቤት በይፋ ሥራ አስጀመረ።
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል የጽህፈት ቤቱን ሥራ ማስጀመር አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ በህወሓት ቡድን አምባገነንነት የፖለቲካ ፓርቲዎች በትግራይ ክልል ቢሮ ከፍተው መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ እንደነበር ገልጸዋል።
ጁንታው ተወግዶ በትግራይ ክልል ለውጥ በመምጣቱ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች ህጋዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ምቹ ሁኔታ አሁን ላይ መፈጠሩን አስረድተዋል።
“ሌሎች ህጋዊ ፓርቲዎችም በተመሳሳይ መንቀሳቀስ የሚችሉበት እድል ተፈጥሯል” ያሉት አቶ ነቢዮ ስሁል ሚካኤል፤ በትግራይ ክልል የተጀመረው የለውጥ ምዕራፍ ህዝቡን የሚያሳትፍና ወጣቱን በግንባር ቀደምትነት የለወጡ አራማጅ የሚያደርግ ነው ብለዋል።