ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም የሀገሬና የዘመዶቼ ነገር ያሳስበኛል አሉ፤ ስለማይካድራም ሆነ ስለ ስለሰሜን...

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም የሀገሬና የዘመዶቼ ነገር ያሳስበኛል አሉ፤ ስለማይካድራም ሆነ ስለ ስለሰሜን ጦር ጥቃት አልተናገሩም

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት የቀሩትን የፈረንጆች 2020 በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ላይ “ኮቪድ አልበቃ ብሎ እኔ ደግሞ የግል ህመም አለብኝ። ስለ አገሬ እጨነቃለሁ” ሲሉ የተደመጡት የህወሓት አባሉ ቴዎድሮስ አድኃኖም፤ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

“አገሬ ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ናት።  በትውልድ አገሬ ትግራይ እየተካሄደ ያለው አስከፊ ጦርነት ያስጨንቀኛል” ያሉትና በህወሓት ላይ የሚወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ እንዲቆም ዓለም ዐቀፍ ግፊት እንዲደረግ ያሳሰቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም፤  ታናሽ ወንድማቸውን ጨምሮ ሌሎች የቤተሰብ አባሎች የት እንዳሉ እንደማያውቁና በስልክ ማግኘት አለመቻላቸውን ጠቅሰዋል።
ንግግራቸውን አስመልክቶ በርካታ አስተያይቶች እየተስተናገዱ ሲሆን በግል ቤተሰቦቻቸው ጋር የነበራቸውን አለመገናኘት እንደ አንድ ግለሰብ አሳዛኝ መሆኑን ለኢትዮጵያ ነገ የገለጹ አስተያየት ሰጭ የግንኙነት እና የስልክ መስመሮች በተከፈቱበት ወቅት ዶ/ር ቴዎድሮስ ጉዳዩን ሳያብራሩ መግለጻቸው አሁንም ለዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ያስተላለፉትን የጨረፍታ መልእክት ያመላክታል ብልዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ በማይካደራ ለደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋም ሆነ በሰሜን እዝ ላይ ለተቃጣው ጥቃትና ክህደት ምንም አይነት የጠራ ምልከታቸውን እስካሁን የተናገሩት ነገር አለመኖሩ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY