በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ዳግም ተጀመረ

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ዳግም ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በጁንታው ላይ እየተወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ ተከትሎ በትግራይ ክልል ለመቋረጥ የተገደደው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ዳግም መጀመሩ ተሰማ።

የፌደራል መንግሥቱ የአዲሱን የገንዘብ ኖት ቅያሪ በማስመልከት ከብሔራዊ ባንክ የወጣ ገንዘብ ወደ ትግራይ በላከበት ወቅት ፤ የህወሓት ጦር በመቀሌ ኤርፖርት የገንዘብ ዘረፋውን ለማካሄድ ጥረት አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።
በዛው ቀን በሰሜን እዝ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጁንታው ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት ተቋርጦ የነበረው የብር ቅያሬ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY