ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የደረሰውን የማንነት ጥቃት ተከትሎ በርካታ ንጹሐን ዜጎች ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ላይ መሆናቸው ተሰማ።
ባለፈው ሳምንት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ከ20 ሺኅ በላይ ሰዎች ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
በመተከል ዞን ቀደም ሲል ከዚህ ቀደም የደረሰውን የታጣቂዎች ጥቃት ተከትሎ በተለያዮ ጊዜያት ወደ አማራ ክልል የሚሸሹና በመጠለያ ጣቢያዎች ለመኖር የተገደዱ ሰዎች ቢኖሩም የአሁኖቹ ተፈናቃዮች ቁጥር ግን በእጅጉ ከፍተኛ ነው ተብሎለታል።
የአማራ ክልል ለተፈናቃዮቹ የተለያዩ ድጋፎችን እያቀረበ መሆኑን ጠቁሞ ሆኖም ከተረጂዎቹ ቁጥር አንጻር የተለያዮ የመንግሥትና የግል ተራድኦ ድርጅቶች ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።