ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ፤ ቦርዱ ቀጣዩ ምርጫ ቀደም ሲል ከተካሄዱ ምርጫዎች ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል።
ምርጫው ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ዓለም ዐቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ቁሳቁሶች 90 በመቶ ተገዝተው መጠናቀቃቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጇ፣ የተገዙት የምርጫ ቁሳቁሶቹና ኅትመቶች ከዚህ በፊት ምርጫ ከተደረገባቸው ቁሳቁሶችና ኅትመቶች የተሻሉና ዓለም ዐቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ አስረድተዋል።
የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹና የመራጭ ካርዶቹ ደግመው መታተም የማይችሉ፣ ከተነካኩ የሚያስታውቁ፣ የራሳቸው የሆነ ቀሪ ያላቸው፣ ኮፒ ለመደረግ የሚያስቸግሩ እንዲሁም የድምጽ መስጫ ሳጥኖቹ አስተማማኝና መራጩ ድምጽ ሲሰጥ በነጻነት ለመስጠት የሚያስችል መከለያዎች ያሉት ነው ተብሎለታል።