አርባ ምንጭ ዮንቨርስቲ 87 የሕክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

አርባ ምንጭ ዮንቨርስቲ 87 የሕክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ  87 የሕክምና ዶክተሮችን ዛሬ ማስመረቁን ይፋ አደረገ።

ከተመራቂዎች ውስጥ 32ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ ዩኒቨርሲቲው የሕክምና ዶክተሮችን ማሰልጠን የጀመረው በዘርፉ ያለውን የባለሙያ እጥረት ለመቅረፍ ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ አስረድቷል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ተመራቂዎች ከፊታቸው የተመራቂዎቹን  አገልግሎት የሚጠብቁ ዜጎች እንዳሉ በመገንዘብ ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ከወዲሁ ሊዘጋጁ ይገባል ሲሉም ምክር ለግሰዋል።
ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ የሕክምና ዶክተሮችን ማሰልጠን የጀመረው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የዛሬውን ጨምሮ በሠባት ዙሮች እስካሁን 572 የሕክምና ዶክተሮችን አስመርቋል።

LEAVE A REPLY