ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከህወሓት ሹማምንቶቹና ወታደራዊ መኮንኖቹ መካከል የቤተክርስቲያን አባቶችን አልባሳት ለብሰው የተገኙ መኖራቸውን የመከላከያ ሰራዊት መግለጫ አመላከተ።
የተደበቁ የህወሓት አመራሮች ከማንም ጋር የሚገናኙበት ዕድል እንደሌላቸውም አስረድቷል።
የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔርን ጨምሮ የትግራይ ክልል ኦዲት ሓላፊ የነበሩት ሃዱሽ ዘውገ ገዛኸኝ፣ የክልሉ ልማት ሥልጠና ሓላፊ የነበሩት አቶ ሰለሞን ህሉፍ ንጉሤ፣ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ የነበሩት አቶ ኪዳነማሪያም ገብረክርስቶስ ፋሲል ለመከላከያ ሠራዊት እጅ መሰጠታቸው ተገለጿል።
ከእነዚህ አመራሮች በተጨማሪ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሓላፊ የነበሩት አቶ ባህታ ወልደሚካኤል፣ የክልሉ ኢኮኖሚ ቢሮ የልማት እቅድ አስተባባሪ አቶ ሀጎስ ወልደኪዳን ገብረማሪያምና የመቀለ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆኑት አቶ ገብረአምላክ ይኸብዮም እጅ ከሰጡት የህወሓት አመራሮች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።
በትግራይ ውስጥ ሆኖ ጥቃት ሲፈጽም ከነበረው የህወሓት ጁንታ ውስጥ ሆነው ጦርነት ውስጥ ከተሳተፉት መካከል ዶክተር ዓለም ብርሃኔ፣ ኮሎኔል መብርሃቱ ገብረመድኅን፣ ኮሎኔል ሃዱሽ ሃጎስ፣ ኮሎኔል ህሉፍ ተ/መድኅን፣ ሌተናል ኮሎኔል ተክለ ህይወት አሰፋ መማረካቸው ዛሬ ይፋ ተደርጎል።